"እጄን እሰጣለሁ" አቶ ልደቱ ማክሰኞ ግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም

 


አቶ ልደቱ አያሌው ወደ ኢትዮጵያ በመመለስና እጃቸውን በሽብርተኝነት ለከሳሳቸው መንግስት እጃቸውን በመስጠት በፍትህ አደባባይ እንደሚሟገቱ አሳወቁ።

በዚህ ጉዳይ በፃፉት ረጅም ፅሁፍ የሚከተውን ብለዋል 

ከአገዛዙ አፈና፣ እስርና ግድያ ሸሽቶ በማምለጥ የሚመጣ መፍትሄ የለም። ትግላችን ሰላማዊና ህጋዊ እስከሆነ ድረስ በገፍ እየታሰርንና እየሞትን አገዛዙ በሀይልና በአፈና ሊያሸንፈን እንደማይችል ተስፋ ልናስቆርጠው ይገባል። በዚህ መጠን ዋጋ ለመክፈል ካልቆረጥን በስተቀር የአገርና የህዝብ ህልውና ከጥፋት ሊድን አይችልምና።

ይህንን በለጋ የልጅነት ዘመኔ ለራሴ የገባሁትን የትግል ቃል-ኪዳንና የምታመንለትን የሰላማዊነትና ህጋዊነት መርህ መሰረት በማድረግ ወደ አገሬ ለመመለስና የዶ/ር ዐቢይን የፈጠራ የአሸባሪነት ክስ እንደተለመደው በፍትህ አደባባይ ለመጋፈጥ ወስኛለሁ።

ስለሆነም በታሰርኩ ቁጥር ከእኔ በላይ ስቃዬን የምትሰቃዩ ቤተ-ዘመዶቸ፣ ጓደኞቸ፣ የሃሳብ ደጋፊዎቸና የትግል አጋሮቸ ይህንን ውሳኔዬን የሞኝነት፣ የአጉል ጀብደኝነት ወይም የመንግስትን የጭካኔ ደረጃ በአግባቡ ያለመረዳት ድክመት አድርጋችሁ እንዳታዩብኝና ያልተገባ ጫና እንዳትፈጥሩብኝ በዚህ አጋጣሚ በአክብሮት እማፀናለሁ። ይህንን ውሳኔ በሚገባ አስቤበትና ከልቤ አምኘበት የወሰንኩት ስለሆነ በሞራል ልታግዙኝ ይገባል እንጂ ልታዝኑልኝም ሆነ ልታዝኑብኝ አይገባም እላለሁ። 

Comments

Post a Comment

Popular posts from this blog

ኢቲቪ በሜዳው ተገረፈ! ግንቦት 3 ቀን 2015 ዓ.ም