ኢቲቪ በሜዳው ተገረፈ! ግንቦት 3 ቀን 2015 ዓ.ም



ኢቲቪ በቀጥታ ስርጭት ከሰላም ስምምነቱ ወዲህ ኢንቨስትመንት እየጎረፈ ነው የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ አንድ ምሁርን ከባህርዳር ስቲዲዮ በቀጥታ ስርጭት አስገባ።


ምሁሩ የሰላም ስምምነቱን በመልካም ጎን  ገልፆ፣ በአንድ በኩል የሰላም ስምምነት እየተባለ በሌላ በኩል ጦርነት መቀስቀስ አያስፈልግም በሚል አስረዳ። አማራ ክልል ላይ እየተደረገ ያለውን ገልፆ በዚህ ምክንያት ኢንቨስትመንት ሊመጣ እንደማይችል፣ ለኢትዮጵያም አደገኛ እንደሆነ አብራራ። ቀጥታ ስርጭት ስለሆነ እንጅ ይህን እውነት አይታገሱም ነበር። በቀጥታ ስርጭትም ቢሆን ሀሳቡን ሳይጨርስ አቋርጠውታል። በቂ እውነት ግን አስተላልፏል። ኢቲቪ ሌላ ትርክት ሊያመጣ ሲል ነው በሜዳው በእውነት ጅራፍ የቀመሰው።

Comments