Posts

ኢቲቪ በሜዳው ተገረፈ! ግንቦት 3 ቀን 2015 ዓ.ም

Image
ኢቲቪ በቀጥታ ስርጭት ከሰላም ስምምነቱ ወዲህ ኢንቨስትመንት እየጎረፈ ነው የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ አንድ ምሁርን ከባህርዳር ስቲዲዮ በቀጥታ ስርጭት አስገባ። ምሁሩ የሰላም ስምምነቱን በመልካም ጎን  ገልፆ፣ በአንድ በኩል የሰላም ስምምነት እየተባለ በሌላ በኩል ጦርነት መቀስቀስ አያስፈልግም በሚል አስረዳ። አማራ ክልል ላይ እየተደረገ ያለውን ገልፆ በዚህ ምክንያት ኢንቨስትመንት ሊመጣ እንደማይችል፣ ለኢትዮጵያም አደገኛ እንደሆነ አብራራ። ቀጥታ ስርጭት ስለሆነ እንጅ ይህን እውነት አይታገሱም ነበር። በቀጥታ ስርጭትም ቢሆን ሀሳቡን ሳይጨርስ አቋርጠውታል። በቂ እውነት ግን አስተላልፏል። ኢቲቪ ሌላ ትርክት ሊያመጣ ሲል ነው በሜዳው በእውነት ጅራፍ የቀመሰው።

"እጄን እሰጣለሁ" አቶ ልደቱ ማክሰኞ ግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም

Image
  አቶ ልደቱ አያሌው ወደ ኢትዮጵያ በመመለስና እጃቸውን በሽብርተኝነት ለከሳሳቸው መንግስት እጃቸውን በመስጠት በፍትህ አደባባይ እንደሚሟገቱ አሳወቁ። በዚህ ጉዳይ በፃፉት ረጅም ፅሁፍ የሚከተውን ብለዋል  ከአገዛዙ አፈና፣ እስርና ግድያ ሸሽቶ በማምለጥ የሚመጣ መፍትሄ የለም። ትግላችን ሰላማዊና ህጋዊ እስከሆነ ድረስ በገፍ እየታሰርንና እየሞትን አገዛዙ በሀይልና በአፈና ሊያሸንፈን እንደማይችል ተስፋ ልናስቆርጠው ይገባል። በዚህ መጠን ዋጋ ለመክፈል ካልቆረጥን በስተቀር የአገርና የህዝብ ህልውና ከጥፋት ሊድን አይችልምና። ይህንን በለጋ የልጅነት ዘመኔ ለራሴ የገባሁትን የትግል ቃል-ኪዳንና የምታመንለትን የሰላማዊነትና ህጋዊነት መርህ መሰረት በማድረግ ወደ አገሬ ለመመለስና የዶ/ር ዐቢይን የፈጠራ የአሸባሪነት ክስ እንደተለመደው በፍትህ አደባባይ ለመጋፈጥ ወስኛለሁ። ስለሆነም በታሰርኩ ቁጥር ከእኔ በላይ ስቃዬን የምትሰቃዩ ቤተ-ዘመዶቸ፣ ጓደኞቸ፣ የሃሳብ ደጋፊዎቸና የትግል አጋሮቸ ይህንን ውሳኔዬን የሞኝነት፣ የአጉል ጀብደኝነት ወይም የመንግስትን የጭካኔ ደረጃ በአግባቡ ያለመረዳት ድክመት አድርጋችሁ እንዳታዩብኝና ያልተገባ ጫና እንዳትፈጥሩብኝ በዚህ አጋጣሚ በአክብሮት እማፀናለሁ። ይህንን ውሳኔ በሚገባ አስቤበትና ከልቤ አምኘበት የወሰንኩት ስለሆነ በሞራል ልታግዙኝ ይገባል እንጂ ልታዝኑልኝም ሆነ ልታዝኑብኝ አይገባም እላለሁ። 

ዐቢይ አህመድ አይተኬ መሪ ናቸውን

Image
  መግቢያ ፦ ባለፉት አምስት ዓመታት በሀገራችን የታየው የፖለቲካ ሂደት ከመቼውም ጊዜ በላይ መርህየለሽ የሆነ የጎራ መደበላለቅ የታየበት ነበር። በተለይም “ዐቢይ አሻጋሪያችን ነው” በማለት በዶ/ር ዐቢይ ዙሪያ ተሰባስቦ የጦርነቱ ዋና ደጋፊና ተዋናይ ሆኖ የታየው የፖለቲካ ጎራ የጋራ ጠላት እንጂ ከህዝብ ጥቅም ጋር የተያያዘ የጋራ የፖለቲካ አጀንዳ ስላልነበረው የሀገሪቱን የፖለቲካ የኃይል አሰላለፍ ቅጥ-አልባ አድርጎት ቆይቷል። ቀደም ሲል ከእነ አቦይ ስብሃት ከእስር መፈታት ጋር ተያይዞ፣ ከዚያም የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ሲፈረምና የሰሜኑ ጦርነት ሲቆም ይህንን መርህ-የለሽ ጎራ አስተሳስሮት የነበረው “የጋራ ጠላት” አጀንዳ ከመኖር ወደ አለመኖር ተቀይሯል። በዚህም ምክንያት የአምስት ዓመቱ የጎራ መደበላለቅ ወደ እውነተኛ ፈርጁ ማለትም ወደ ቅድመ 2010 ዓ.ም ተመልሶ ሲሸጋሸግ እያየን ነው። ከጦርነቱ መቆም በኋላ የኃይል አሰላለፍ ለውጥ እየመጣ እንደሆነ ምልክቶች ሲታዩ የነበረ ቢሆንም የመጣው ለውጥ ራሱን በጎላ ሁኔታ የመግለፅ ዕድል ያገኘው ግን ከወቅቱ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ችግር ጋር ተያይዞ ነው ማለት ይቻላል። ማለትም መንግስት በቤተክርስቲያኗ ላይ ያሳየው አይን ያወጣ ጣልቃ-ገብነት ቀድሞውንም ጎራቸውን ለመለየት ዳርዳርታ ላይ ለነበሩ የፖለቲካ ኃይሎችና ግለሰቦች ወደ እውነተኛው ጎራቸው ለመሸጋገር ጥሩ ሰበብና ዕድል የፈጠረላቸው አጋጣሚ ሆኗል። “ጊዜ እንስጠው”፣ “ሌሎች አላሰራ ብለውት ነው”፣ “የባሰ አደጋ እንዳይመጣብን ብለን ነው” ወዘተ… በሚሉ አመክንዮ-አልባ ሰበቦች ዶ/ር. ዐቢይን በጭፍን ሲደግፉ የነበሩ ሁሉ ዛሬ ላይ ቀንደኛ የዶ/ር ዐቢይ ተቃዋሚ በመሆን የሸሚዛቸውን እጄታ ሲሰበስቡ እያየን ነው። ይህ ለውጥ በሰሞኑ የአድዋ በዓል አከባበር ምክንያትም የ

እሁድ ሚያዝያ 15 2015 “ጦርነት ይብቃ ሰላምን እናጽና” በሚል መሪ ቃል በወዳጅነት አደባባይ ስለተካሄደው ወለፈንዴ ተወኔት የግል ምልከታ -- አንዳርጋቸው ጽጌ

Image
  አንድ ከሀገርና ከህዝብ ክብር ጋር የተሳሰረች ነፍስ ያለው ሰው፣ የሃገሩን እና የህዝቡን ክብር ማስከበር ካቃተው የራሱን ክብር ያስከብራል። ምን ማድረግ ይቻላል በሚል ተልካሻ ምክንያት ራሱን ለውርደት አሳልፎ አይሰጥም። “ጊዜ እስኪያልፍ ........ “ የሚለውን የሆዳሞች ተረት እየተረተ ትወልድ የሚያፍርበትን ስራ ሲሰራ አይታይም። ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲህ አይነቱ ከግለሰቦች ሰብአዊ ክብር ጋር የተያያዘው የቆየው ባህላችን እየጠፋ ነው። ጥቅምንና ስልጣን እያሰላሉ የራስንና የህዝብን ክብር እየሸጡ፣ ነገር ግን የያዙትን እርባና ቢስ አቋም ከከፍተኛ የሞራል ማማ ላይ ተቁሞ እንደተያዛ አቋም አድርገው ራሳቸውን ሸንገለው ሌላውን ለመሸንገል የሚሞክሩ አሳዛኝ ፍጥረቶች የሃገራችን የፖለቲካ ምህዳር እንደ ተምች ሰፍረውበታል። በእንዲህ አይነቱ ሃገር፣ የፍትህ፣ የሞራልና የመብት ጥያቄዎች የሚያነሱ የስርአቱ የአፈናና የጥቃት ሰለባ እንደሚሆኑና እየሆኑ እንደሆነ ይታያል። ከጥቂት አመታት በፊት የፈነጠቀው የለውጥ ተስፋ የሰቆቃ እና የሲቃ፣ የዘረፋና የገፈፋ ዘመን እንዳበቃ የጠቆመን መስሎን ነበር። የተንጠለጠልነው በቀቢጸ ተስፋ ላይ እንጂ በእውነተኛ ተስፋ ላይ አለመሆኑ መረጃዎቹ እየተበራከቱ መጥተዋል። ይህ እያዩ እንዳላዩ ማለፍ ለእንደኔ አይነቱ ሰው ከነውርም በላይ ነውር ነው። ሰላም የሁሉ ነገር መሰረት መሆኑን እኔም በግሌ በተደጋጋሚ ተናግሬያለሁ። ጽፌያለሁ። የሃገርና የህዝብ ሰላም ከሚደፈርስ በኢትዮጵያን፣ የኦህዴድ እና የድህዴን ወንጀለኛ ባለስልጣናትንማ ስማቸውንም አንስቼ አላውቅም። እኔ ብቻ አይደለሁም አብዛኛው የሃገራችን ህዝብ ለሰላም ሲል መከፈል የሚገባውን ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ ሆኖ ነበር። “በወያኔ የግፍ ዘመን የተገደለውን ሁሉ የኢትዮጵ ህዝብ ላይ እጅግ አሰቃ