Posts

Showing posts from May, 2023

ኢቲቪ በሜዳው ተገረፈ! ግንቦት 3 ቀን 2015 ዓ.ም

Image
ኢቲቪ በቀጥታ ስርጭት ከሰላም ስምምነቱ ወዲህ ኢንቨስትመንት እየጎረፈ ነው የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ አንድ ምሁርን ከባህርዳር ስቲዲዮ በቀጥታ ስርጭት አስገባ። ምሁሩ የሰላም ስምምነቱን በመልካም ጎን  ገልፆ፣ በአንድ በኩል የሰላም ስምምነት እየተባለ በሌላ በኩል ጦርነት መቀስቀስ አያስፈልግም በሚል አስረዳ። አማራ ክልል ላይ እየተደረገ ያለውን ገልፆ በዚህ ምክንያት ኢንቨስትመንት ሊመጣ እንደማይችል፣ ለኢትዮጵያም አደገኛ እንደሆነ አብራራ። ቀጥታ ስርጭት ስለሆነ እንጅ ይህን እውነት አይታገሱም ነበር። በቀጥታ ስርጭትም ቢሆን ሀሳቡን ሳይጨርስ አቋርጠውታል። በቂ እውነት ግን አስተላልፏል። ኢቲቪ ሌላ ትርክት ሊያመጣ ሲል ነው በሜዳው በእውነት ጅራፍ የቀመሰው።

"እጄን እሰጣለሁ" አቶ ልደቱ ማክሰኞ ግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም

Image
  አቶ ልደቱ አያሌው ወደ ኢትዮጵያ በመመለስና እጃቸውን በሽብርተኝነት ለከሳሳቸው መንግስት እጃቸውን በመስጠት በፍትህ አደባባይ እንደሚሟገቱ አሳወቁ። በዚህ ጉዳይ በፃፉት ረጅም ፅሁፍ የሚከተውን ብለዋል  ከአገዛዙ አፈና፣ እስርና ግድያ ሸሽቶ በማምለጥ የሚመጣ መፍትሄ የለም። ትግላችን ሰላማዊና ህጋዊ እስከሆነ ድረስ በገፍ እየታሰርንና እየሞትን አገዛዙ በሀይልና በአፈና ሊያሸንፈን እንደማይችል ተስፋ ልናስቆርጠው ይገባል። በዚህ መጠን ዋጋ ለመክፈል ካልቆረጥን በስተቀር የአገርና የህዝብ ህልውና ከጥፋት ሊድን አይችልምና። ይህንን በለጋ የልጅነት ዘመኔ ለራሴ የገባሁትን የትግል ቃል-ኪዳንና የምታመንለትን የሰላማዊነትና ህጋዊነት መርህ መሰረት በማድረግ ወደ አገሬ ለመመለስና የዶ/ር ዐቢይን የፈጠራ የአሸባሪነት ክስ እንደተለመደው በፍትህ አደባባይ ለመጋፈጥ ወስኛለሁ። ስለሆነም በታሰርኩ ቁጥር ከእኔ በላይ ስቃዬን የምትሰቃዩ ቤተ-ዘመዶቸ፣ ጓደኞቸ፣ የሃሳብ ደጋፊዎቸና የትግል አጋሮቸ ይህንን ውሳኔዬን የሞኝነት፣ የአጉል ጀብደኝነት ወይም የመንግስትን የጭካኔ ደረጃ በአግባቡ ያለመረዳት ድክመት አድርጋችሁ እንዳታዩብኝና ያልተገባ ጫና እንዳትፈጥሩብኝ በዚህ አጋጣሚ በአክብሮት እማፀናለሁ። ይህንን ውሳኔ በሚገባ አስቤበትና ከልቤ አምኘበት የወሰንኩት ስለሆነ በሞራል ልታግዙኝ ይገባል እንጂ ልታዝኑልኝም ሆነ ልታዝኑብኝ አይገባም እላለሁ።