ዐቢይ አህመድ አይተኬ መሪ ናቸውን
መግቢያ ፦ ባለፉት አምስት ዓመታት በሀገራችን የታየው የፖለቲካ ሂደት ከመቼውም ጊዜ በላይ መርህየለሽ የሆነ የጎራ መደበላለቅ የታየበት ነበር። በተለይም “ዐቢይ አሻጋሪያችን ነው” በማለት በዶ/ር ዐቢይ ዙሪያ ተሰባስቦ የጦርነቱ ዋና ደጋፊና ተዋናይ ሆኖ የታየው የፖለቲካ ጎራ የጋራ ጠላት እንጂ ከህዝብ ጥቅም ጋር የተያያዘ የጋራ የፖለቲካ አጀንዳ ስላልነበረው የሀገሪቱን የፖለቲካ የኃይል አሰላለፍ ቅጥ-አልባ አድርጎት ቆይቷል። ቀደም ሲል ከእነ አቦይ ስብሃት ከእስር መፈታት ጋር ተያይዞ፣ ከዚያም የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ሲፈረምና የሰሜኑ ጦርነት ሲቆም ይህንን መርህ-የለሽ ጎራ አስተሳስሮት የነበረው “የጋራ ጠላት” አጀንዳ ከመኖር ወደ አለመኖር ተቀይሯል። በዚህም ምክንያት የአምስት ዓመቱ የጎራ መደበላለቅ ወደ እውነተኛ ፈርጁ ማለትም ወደ ቅድመ 2010 ዓ.ም ተመልሶ ሲሸጋሸግ እያየን ነው። ከጦርነቱ መቆም በኋላ የኃይል አሰላለፍ ለውጥ እየመጣ እንደሆነ ምልክቶች ሲታዩ የነበረ ቢሆንም የመጣው ለውጥ ራሱን በጎላ ሁኔታ የመግለፅ ዕድል ያገኘው ግን ከወቅቱ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ችግር ጋር ተያይዞ ነው ማለት ይቻላል። ማለትም መንግስት በቤተክርስቲያኗ ላይ ያሳየው አይን ያወጣ ጣልቃ-ገብነት ቀድሞውንም ጎራቸውን ለመለየት ዳርዳርታ ላይ ለነበሩ የፖለቲካ ኃይሎችና ግለሰቦች ወደ እውነተኛው ጎራቸው ለመሸጋገር ጥሩ ሰበብና ዕድል የፈጠረላቸው አጋጣሚ ሆኗል። “ጊዜ እንስጠው”፣ “ሌሎች አላሰራ ብለውት ነው”፣ “የባሰ አደጋ እንዳይመጣብን ብለን ነው” ወዘተ… በሚሉ አመክንዮ-አልባ ሰበቦች ዶ/ር. ዐቢይን በጭፍን ሲደግፉ የነበሩ ሁሉ ዛሬ ላይ ቀንደኛ የዶ/ር ዐቢይ ተቃዋሚ በመሆን የሸሚዛቸውን እጄታ ሲሰበስቡ እያየን ነው። ይህ ለውጥ በሰሞኑ የአድዋ በዓል አከባበር ምክንያትም የ